HealthFlex
×
  • Home
  • who we are
  • What We Do
    • Providing Trainings
    • Consultancy Services
    • Catering & Lodging Service
    • Training Facility
      • Big Conference Room
      • Medium Hall
      • Syndicate Room
      • Training Room I
      • Training Room 2
      • Training Room 3
    • Fitness & Wellness Service
  • Announcements & Publication
    • Training Catalogue
    • Call for training
    • Gallery
  • Book Now
  • Contact us

እናቶች በኢቀመማ በኩል ለተፈናቃዮች መርጃ የሚሆን የ150,000 ብር ድጋፍ አደረጉ

April 17, 2019
የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 እናቶች “የተጎዳን ለመርዳት እናት መሆን በቂ ነው” በሚል መሪ ቃል ለተፈናቃይ ወገኖች መርጃ የሚሆን 150,000 ብር እና የተለያዩ አልባሳትን በማሰባሰብ ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ሚያዝያ 05 ቀን 2011 ዓ.ም አበርክተዋል፡፡ ድጋፉን የእርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ ሶሪት ከሊፋ ለማኅበሩ ቦርድ አባል አምባሳደር ዶ/ር ቶፊቅ አብዱላሂ አስረክበዋል፡፡
 
በስነ-ስርዓቱ ላይ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ ሀመረ ታደገ እንደተናገሩት፣ ይህ በጥቂት እናቶች የተጀመረውን እንቅስቃሴ በማስፋትና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ እንዲሁም ባለሀብቶችና ድርጅቶች ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ በማድረግ በቀጣይ እንቅስቃሴ የሚደረግ ይሆናል፡፡
 
“እናቶቹ የበጎ አድራጎት ሥራውን ለማከናወን ሶስት ዓመታትን የሚሸፍን ራዕይ ቀርፀው ወደ ተግባር ለመግባት የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን እያከናወኑ ነው” ያሉት ወ/ሮ ሀመረ፣ “የዛሬዋ ዕለትም ቀጣይ እቅዳችንን የምናሳውቅበት፣ ለወጣት ልጆቻችን የእናትነት የሰላም ጥሪ የምናስተላልፍበት እንዲሁም በአደጋ ምክንያት ደም ለሚያሻቸው ወገኖቻችን የደም ልገሳ የምናደርግበት ነው” ብለዋል፡፡
 
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የቦርድ አባል አምባሳደር ዶ/ር ቶፊቅ አብዱላሂ በበኩላቸው፣ የወረዳው እናቶች ያከናወኑት ተግባር ሌሎች እናቶችንም የሚያነሳሳና ትልቅ አርዓያ መሆኑን ተናግረው፣ “የሰበሰባችሁት እርዳታ ለተፈናቃይ ወገኖች በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በኩል እንዲደርስላችሁ ስላደረጋችሁ ኮርተንባችኋል” ብለዋል፡፡
 
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ለተጋለጡ ወገኖች የሚሰጠውን ሰብዓዊ አገልግሎት በይበልጥ ለማስፋት የበጎ ፈቃደኞቹ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የአካባቢው ማኅበረሰብ የማህበሩ በጎ ፈቃደኛና አባል በመሆን ድጋፍ እንዲያደርግ አምባሳደር ዶ/ር ቶፊቅ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
 
በተደረገው ገንዘብ ማሰባሰብ ላይ 170 የሚሆኑ እናቶች መዋጮ በማድረግ የተሳተፉ ሲሆን በዕለቱ የአካባቢው ነዋሪዎች የደም ልገሳ አድርገዋል፡፡

Add Comment Cancel


Ever wondered what ERCS CCDHS Provides?

Visit our Training Facility!

Calendar

April 2019
M T W T F S S
1234567
891011121314
15161718192021
22232425262728
2930  
« Mar   May »

Categories

  • News

Tag Cloud

Front Page

Contact Us

Ethiopian Red Cross Society-Training Institute, Nifas Silk Lafto Sub City, Woreda 10, Debrezite Road, 400 meter right to Aday Ababa Textile & Garment Factory.

+251-11-442-02-35

ERCS-TI@redcrosseth.org

Ethiopian Red Cross Society Triaining Institute

Quick Links

  • Call for training
  • Providing Trainings
  • Training Catalogue

FOLLOW US

  • Facebook
  • YouTube
  • X
  • Telegram
  • Flickr
Copyright ©2025 | All Rights Reserved
Designed and Developed By Rackmint System